June 20, 2018
ዶ/ር ዳንኤል ተፈራ፤ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር፤ ኤመረተስ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር፤ ዶ/ር አቢይ አህመድ፤ በ6/18/18 ከህዝብ ተወካዮች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡትን መልስ አዳምጫለሁ። ጠቅላይ ምኒስትሩ ለሰጡት መልስና ላቀረቡት ገለጻ አስተያየቴን እንደሚከተለው ለማቅረብ አወዳለሁ። አንደኛው የመደመር ፖለቲካ ያሉት ላይ ያተኩራል። ጠቅላይ ምኒስትሩ ሀገሪቱ አሁን የደረሰችበት ሁኔታ አደገኛ በመሆኑ የሀሳብ ልዩነቶች በሰላማዊና በቀና መንፈስ እንዲስተናገዱ ሀሳብ አቅርበዋል። ይህን ሀሳብ ያቀረቡት፤...